Oct 15, 2022
अबा त्सिगे डेंगल ने "महलेते त्सिगे" निबंध लिखा था। पुराने संस्करण डाउनलोड और इंस्टॉल करें ማህሌተ ጽጌ जो आपके डिवाइस मॉडल के अनुकूल है और अपनी पसंदीदा सुविधाओं का आनंद लें!
በ5ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምስቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መ.ክ.ዘመን የተነሣው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል “ማኅሌተ ጽጌ” የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሔድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውለው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊት በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እያሰቡ የሚደረስ ምሥጋናና ጸሎት ነው፡፡