Use APKPure App
Get ነቅረእ - 01 የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01) old version APK for Android
ነቅረእ- 01 አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን አፕልኬሽን
ነቅረእ-01 የሞባይል አፕልኬሽን በረጅም ጊዜ ጥናት በነቅረእ ዘመናዊ የቁርኣን ንባብ ት/ቤት የተዘጋጀ ቁርኣን ውስጥ የዐረብኛ ፊደላትን በቀላሉ ማወቅና መለየት እንድንችል የሚያስተምር እጅግ ዘመናዊ የሞባይል አፕልኬሽን ነው፡፡
አፕልኬሽኑ ለተጠቃሚዎች ምቹ እና ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ ተያያዥ በሆኑ አራት ክፍሎች ተከፍሏል፡፡
ክፍል አንድ፡ የዐረብኛ ፊደላትን በግርድፉ መለየት
በዚህ ክፍል ተጠቃሚው ከሀያ ስምንቱ የዐረብኛ ፊደላት ጋር የመጀመሪያ ትውውቅ ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ የዐረብኛ ፊደል የሚለይበት ነገራት ተጠቅሰው ፊደላትን በግርድፉ የመለየት ትምህርት በጥልቀት ይሰጣል፡፡ ይህ ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል ሀያ ስምንቱንም የዐረብኛ ፊደላት በግርድፉ ለመለየት በምስል ፡ በጽሑፍና በድምጽ በታገዝ ሁኔታ በደንብ የተብራራ ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ደግሞ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች ተካተዋል፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ሁለት ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ ቀጣይ ክፍል ሁለት ይከፈትሎታል፡፡
ክፍል ሁለት፡ የዐረብኛ ፊደላት የድምጽ አወጣጥ
በዚህ ክፍል የሀያ ስምንቱ የዐረብኛ ፊደላት የድምጽ አወጣጥ ትምህርት በዝርዝርና በጥልቀት ይሰጣል ፡፡ እያንዳንዱን የዐረብኛ ፊደል ከአማርኛ ፊደላት የድምጽ አወጣጥ ጋር በማነጻጸር ትክክለኛ የድምጽ አወጣጡን የማወቅና የማውጣት ትምህርት በጥልቀት ይሰጣል፡፡ ይህም ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል የሀያ ስምንቱን የዐረብኛ ፊደላት ትክክለኛ የድምጽ አወጣጥ በምስል፡ በጽሑፍና በድምጽ በታገዝ ሁኔታ በደንብ የተብራራ ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ደግሞ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች ተካተዋል፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ሶስት ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ ቀጣይ ክፍል ሶስት ይከፈትሎታል፡፡
ክፍል ሶስት፡ የዐረብኛ ፊደላት የአቀጣጠል ሁኔታ
በዚህ ክፍል ከሀያ ስምንቱ የዐረብኛ ፊደላት የአቀጣጠል ሁኔታና ቅርጽ ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጣል፡፡ እያንዳንዱ የዐረብኛ ፊደል የዐረብኛ ቃላት ውስጥ ተቀጣጥሎ በሚመጣበት ጊዜ እንዴት በቀላሉ መለየት እንደምንችል የሚያግዘን ትምህርት በስፋትና በጥልቀት ተካቷል፡፡ ይህም ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል ሀያ ስምንቱንም ፊደላት በዐረብኛ ቃላት ውስጥ ተቀጣጥለው ሲመጡ በቀላሉ የመለየት ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ደግሞ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስተማሪ ቪዲዮዎች ተካተዋል፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ ቀጣይ ክፍል አራት ይከፈትሎታል፡፡
ክፍል አራት፡ የዐረብኛ ፊደላትን ውስጥ መለየት
በዚህ ክፍል ሀያ ስምንቱን የዐረብኛ ፊደላት ቁርኣን ውስጥ የመለየት ልምምዳዊ ት/ት ይሰጣል ፡፡ አንድ ከቁርኣን የተወሰደ ምዕራፍ ተጠቅሶ በዚያ ምዕራፍ ውስጥ የሚገኙትን የዐረብኛ ፊደላት ባለፉት ሶስት ክፍሎች በተማረው መሰረት ፊደላቱን ቁርኣን ውስጥ የመለየት ተግባራዊ የልምምድ ት/ት ይሰጣል ፡፡ ይህም ክፍል በ 4 ንዑስ ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን እነሱም መማሪያ፡ አጋዥ ቪዲዮዎች፡ መለማመጃ እና ፈተና ናቸው፡፡ በ መማሪያ ክፍል ሀያ ስምንቱንም የዐረብኛ ፊደላት በምሳሌነት በተሰጠው የቁርኣን ምዕራፍ ውስጥ በቀላሉ የመለየት ት/ት ይሰጣል፡፡ በ አጋዥ ቪዲዮዎች ክፍል ምንም ተያያዥ ቪዲዮ አልተካተተም፡፡ በ መልመጃ ክፍል ትምህርቱን በጥያቄና መልስ በደንብ የመለማመድ ስራ ይሰራል፡፡ በ ፈተና ክፍል ደግሞ ተጠቃሚውን ወደ ቀጣይ ክፍል ለማሳለፍ የመመዘኛ ጥያቄዎች ተቀምጠዋል፡ የመመዘኛውን ፈተና ሲያልፉ የዐረብኛ ፊደላት የማወቅና የመለየት ት/ት በአግባቡ መጨረስዎ እርግጥ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ :
Telegram: @neqra
Facebook: neqraquranreadingcenter
+251 911 38 39 49 /+251 911 55 56 76
द्वारा डाली गई
Tauheed T
Android ज़रूरी है
Android 4.1+
श्रेणी
रिपोर्ट
Last updated on Mar 15, 2019
- 1 Lesson free trial
ነቅረእ - 01 የዐረብኛ ፊደላት መማሪያ(Neqra 01)
1.0 by ነቅረእ ዘመናዊ የቁርኣን ንባብ ት/ቤት
Mar 15, 2019